ዓርብ 3 ማርች 2017

 አርማጌዶን ¡ (Thoreau’s Fiery Essay “On the Duty of Civil Disobedience”)


አርማጌዶን ¡
(በተስፋዬ ቀኖ)
(Thoreau’s Essay On Civil Disobedience)
(ምዕራፍ አንድ)
(1) ይህን መፈክር አምንበታለሁ፡- “በቅጡ የሚገዛ መንግሥት ማለፊያ ነው”'(1) እና በፍጥነት እና በሥርዓት እንዲተገበር እሻለሁ' ሲጠቃለል ይህ ነው& እኔም እንደማምነው፣ “---፣ መንግሥት ማለት ፈፅሞ የማይገዛ ቢሆን ማለፊያ ነው”@ ሰዎች ሲዘጋጁበት የሚኖራቸው መንግሥት እሱ ነው' መንግሥት ሲሆን ሲሆን የሚያሰራ መሆን አለበት@ እውነቱ ግን አብዛኛው መንግሥት አብዛኛውን ጊዜ ሁሉም ደግሞ አልፎ አልፎ የማያሰሩ ናቸው' በሠራዊት ያለው ተቃውሞ& በዛ እና ከበድ ያሉ ናቸው& ጎልተውም ሊታዩ የተገባቸው ናቸው* በመንግሥትም ላይ መተግበር ይገባቸዋል' ሠራዊቱ የመንግሥት እጅ እንደማለት ነው' መንግሥት እራሱ ሕዝቡ ፈቃዱን ለመፈፀም የመረጠው መንገድ ሕዝቡ ፈቃዱን ከመፈፀሙ በፊት ሊጣመም እና ከመንገድ ሊወጣ ይችላል' እስኪ ያሣያችሁ የወቅቱን የሜክሲኮ ጦርነት እንውሰድ&(2) መንግሥትን እንደመሣሪያ በመጠቀም ጥቂቶች የሰሩት ሥራ@ ከመነሻው ሕዝቡ በዚህ አድራጎት አይስማማም ነበርና'
(2)ይህ የአሜሪካ መንግሥት --- ልማድ እንጅ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? ዘመነኛ ከመሆኑ በቀር& እራሱን ያለርህራሔ ወጣቱ ትውልድ ላይ ለመጫን የሚጥር& ሆኖም በየደረጃው ታማኝነቱን እያጣ? ያንድ ሰው ያክል እንèን አቅም የለውም@ ምክንያቱም አንድ ሰው እንዳሻው እንደፍላጎቱ ያጣምመዋልና' ልክ ከእንጨት እንደተሰራ የእንጨት ጠብ-መንጃ ማለት ነው' ነገር ግን ከዚህ የተሻለ ፋይዳ አይኖረውም' ሕዝቡ ከዚህ ረቀቅ ያለ መኪና ሊኖራቸውና ሊሰሙ በተገባና የመንግሥት ጥማቸውን በተወጡ ነበር' በመሆኑም መንግሥታት ለራሳቸው ጥቅም ሰዎች ላይ እንዴት ተፅዕኖ ማድረግ እንደሚቻል ወይንም እርስ በርሳቸው ተፅዕኖ ማድረግ እንደሚችሉ የሚያሳዩ መµሪያዎች ናቸው'
ይሁን እንስማማለን@ ሆኖም ይህ መንግሥት ፈፅሞ ከራሱ የመነጨ ሙያ የለውም' ግን መንገዱን ለመሳት በሚያደርገው ጥድፊያ አገርን ነፃ አያወጣ& ምዕራብን አያሰፍር& አንዳችም አያስተምርም'
በአሜሪካውያን ያለው ጥሩ ማንነት እስካሁን የተከናወነውን አድርæል፣ መንግሥት ዕንቅፋት አየሆነ ባያስቸግር የተሻለ በተከናወነ ነበር' ምክንያቱም& መንግሥት ማለት አንዱ ሌላውን ለቀቅ የሚያደርግበት& እንደተባለውም ‘ሚያሰራው ሕዝቡን ለቀቅ ማድረግ ሲችል ነው' ልውውጥና ንግድ ከሕንድ ጎማ (3) ካልተሰሩ በቀር ባለሥልጣኖች በቀጣይነት በመንገዳቸው የሚያኖሩትን እንቅፋት መጋፈጥ አይችሉም' እናም እነዚህን ሰዎች ፍላጎታቸውን ሚዛን ውስጥ ሳናስገባ በተግባራቸው ብቻ እንዳኝ ካልን ባቡር ሐዲድ ላይ እንቅፋት እንደሚያኖሩት እርኩስ ግለሰቦች ሊፈረጁ እና ሊቀጡ በተገባቸው'
(3) ሆኖም እንደዜጋ እና እንደ እውነቱ ለመናገር መንግሥት አያስፈልግም እንደሚሉት(4) በአንዴ መንግሥት ይቅር ሣይሆን& በአንዴ የተሻለ መንግሥት እጠይቃለሁ' እያንዳንዱ ሰው ሊያከብር የሚፈልገው መንግሥት የትኛው እንደሆነ ያሣውቅ& ይህም ራዕዩን ዕውን ለማድረግ አንድ እርምጃ ነው'
(4) እንዲያውም እኮ& ስልጣን በአብላጫው ሕዝብ እጅ ሲገባ& አብላጫው ሕዝብ ስልጣን እንዲኖረው የሚፈቀድበት ትርጉም ያለው ምክንያት ብሎም በቀጣይነት የሚገዛበት ምክንያት ትክክለኞች በመሆናቸው ወይንም ይህ በአናሦች ተቀባይነት ስላገኘ ሳይሆን በጉልበት ስለሚበልጡ ብቻ ነው'
ነገር ግን አብላጫው የሚገዛበት መንግሥት ሁልጊዜ ሰዎች ሊረዱ እስከሚችሉትም ቢሆን እንèን በፍትሕ ላይ የተመሰረተ ሊሆን አይችልም' አብላጮች ከሞላ-ጎደል ትክክል ወይንም ስህተት ብለው መወሰን የማይችሉበት መንግሥት ከቶ ሊኖር አይችልም@ ከኅሊና በቀር? አብላጫው መተግበር የሚችሉ ጉዳዮችን በተመለከተ ብቻ የሚወስኑ ይሆናል? ዜጋው ለአፍታ ወይንም ቢያንስ ቢያንስ ህልውናውን አሳልፎ መስጠት አለበት' እንግዲያውስ እያንዳንዱ ሰው ኅሊና ለምን ኖረው ታዲያ? በቅድሚያ ሰው በመቀጠል ቢያስፈልግ ታማኝ መሆን ይጠበቅብናል' ሕግን ከማክበር ይልቅ የሚበልጠው ለእውነት መታዘዝ ነው' እኔ ብቸኛው ግዴታዬ በማንኛWም ጊዜ ትክክለኛነቱ የገባኝን ነገር ማድረግ ነው' እውነት በበቂ ሁኔታ ተብሎአል' “ድርጅት ኅሊና የለውም@ ሆኖም ኅሊና ያላቸው ሰዎች ያሉበት ድርጅት እርሱ ኅሊና ያለው ነው' ህግ ማንንም ጥቂት እንèን የተሻለ ፍትሐዊ አድርጎ አያውቅም' እናም& በሚሰጡት ከበሬታ ከሕግ ተስማምተው የሚኖሩት በየቀኑ የኢ-ፍትሐዊነት መሣሪያ ይሆናሉ' የተለመደውና ተፈጥሮአዊው ሕግን ያለቅጥ የማክበር ውጤት& ወታደሮች& ጅል-ናሮች& ኮሎኔሎች& ካፒቴኖች& የዱቄት ዝንጀሮዎች(5) እና ሁሉም በሚያስደንቅ ሥርዓት ተሰልፈው በጋራው ወደ ጦርነት በፈቃዳቸው ተቃራኒ፣ አዎን፤ ከስሜታቸውና ከኅሊናቸው ተቃራኒ ሲነጉዱ ማየት ነው' ይህም ሰልፋቸውን እጅግ አቀበታማ ያደርገዋል@ ብሎም ልብን ያሸብራል' በርግጥ ይህ የተጠመዱበት ሁሉም በሠላማዊ መንገድ ራሳቸውን የሰጡት ሙያ የተረገመ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም' አሁን ምን ትሏቸዋላችሁ? ከቶ ሰዎች? ወይስ አንድን የነቀዘ ባለሥልጣን የሚያገለግሉ ተንቀሳቃሽ ምሽጎች? የባህር ኃይልን ግቢ እዩልኝ! የአሜሪካ መንግሥት የፈጠረውን& ወይንም ሊፈጥር የሚችለውን ሰው ከነ አስማቱ ---፣ የሰው ትዝታና ጥላ& የቆመ ግን ደግሞ በቁሙ የተቀበረ& አንዱ ሊል እንደሚችል* ከእጆቹ በታች በቀብር አጃቢዎች& ምንም እንèን ሊሆን ቢችልም*
“ጀግናችንን በቀበርንበት መካነ-መቃብር ላይ&
ያንድም ከበሮ ድምፅ አልተሰማም& ምንም የሕይወት ታሪክ አልተነበበም@
ሙትቻውን ይዘን ወደ ምሽጉ ስንቻኮል&
አንድም ወታደር የስንብት ተኩስ አላሰማም¡”(6)
(5) አብዛኛው ሰው በመሆኑም&መንግሥትን የሚያገለግለው በዋነኝነት እንደ ሰው ሣይሆን& በአካሉ እንደ መኪና ነው' እነሱም ጦር-ሠራዊቱ& ሚሊሻዎች፣ አሣሪዎች፣ ፖሊሶች፣ ደንብ አስከባሪዎችና(7) የመሣሰሉት ናቸው' በአብዛኛው የሞራል ነገር ምዘናም ሆነ ትግበራ አይታሰብም@ ነገር ግን ራሳቸውን ከእንጨት፣ አፈርና ድንጋይ ተርታ ይፈርጃሉ' እናም ከእንጨት ተመጣጣኝ ፋይዳ የሚሰጡ ሰዎችን መፈብረክ ይቻላል' እነኚህ ከሣርና ከቁሻሻ የተሻለ ከበሬታ አይገባቸውም' ከፈረስና ከውሻ ያልተሻለ ዋጋ ‘ሚሰጣቸው ናቸው' ሆኖም፣ እነዚህ በመንግሥት እንደተከበሩ መልካም ዜጎች ይቆጠራሉ' ሌሎች የሕግ ሰዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ዳኞች፣ ሚኒስትሮች፣ እና የቢሮ ሰዎች መንግሥትን በጭንቅላታቸው ያገለግሉታል' እናም የሞራል ምዘና ስለማያደርጉ፣ ሣያስቡት እንደ እግዚአብሔር ሁሉ ዲያብሎስን ማገልገላቸው አይቀሬ ነው' በጣም ጥቂቶች፣ ጀግኖች፣ አርበኞች፣ ሰማዕታት፣ የተሐድሦ ሰዎች፣ እና ሰዎች መንግሥትን በኅሊናቸው ጭምር ያገለግሉታል@ ስለዚህ ብዙውን ጊዜ እምቢ ለማለት ይገደዳሉ@ በመሆኑም በመንግሥት እንደጠላት ይቆጠራሉ' “ጠቢብ ሰው ፋይዳው እንደሰው ብቻ እንጅ ራሱን አሣልፎ ሸክላ ለመሆንና በቀዳዳ የሚገባውን ነፋስ ለማቆም አይኖርም”፣(8) ቢያንስ ስፍራውን ለአፈሩ ይለቃል*
“ለማንኛውም በዚህ ምድር ላለ መንግሥት፣
እንደዕቃ መቆጠር፣
በሌሎች ተፅዕኖ ሥር መዋል፣
ጠቃሚ ሎሌ ወይንም መሣሪያ መሆን፣
አፈጣጠሬን አይመጥንም!”(9)
(6) እራሱን ለወገኑ አሣልፎ የሚሰጥ ዋጋ የሌለውና የራሱን ጥቅም አሣዳጅ ሆኖ ይታያቸዋል@ ራሱን በጥቂት ለእነሱ የሚሰጥ ለጋስ ወይንም ሰብዓዊ ተደርጎ ይቆጠራል'
(7) ይህን የአሜሪካ መንግሥት ሰው ዛሬ እንዴት ሊመለከተው ይችላል? ያለውርደት ሊሆን እንደማይችል አፌን ሞልቼ እናገራለሁ' ይህንን የፖለቲካ ድርጅት ለአፍታም ቢሆን የባሪያ መንግሥት ነውና እንደራሴ መንግሥት አልቆጥረውም'
(8) ማንኛውም ሰው የአብዮትን ተገቢነት ያምናል@ ጭቆናውና ግፉ ሲያይልና መንግሥትን የመቃወምም ሆነ እምቢ የማለትን አብዮት' ነገር ግን፣ ሁሉም ጊዜው ገና አልደረሰም ሲሉ ይደመጣሉ' ግን ጊዜው ደርሷል፣ በ75ቱ አብዮት(10) አንዱ ይህ ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ላይ ግብር ስለጣለ ክፉ መንግሥት ነበር ቢለኝ፣ ሊሆን የሚችለው ስለዚህ ጉዳይ ጭንቀት አይገባኝም፣ ምክንያቱም አይኮነስረኝም¡ እያንዳንዱ መኪና የራሱ ሰበቃ አለው@ የራሱን ክፋት የሚያካክስ በቂ በጎነት ሊኖረው ይችላል' ሆኖም ቢያንስ* Aራስ እያረረ የሌላውን ማማሰሉ ታላቅ ክፋት ነው! ነገር ግን ሰበቃው የራሱ መኪና ሲኖረውና ጭቆናና ወሮ-በላነት ሲደራጁ፣ እላለሁ፣ እንዲህ ዓይነቱን መኪና ከእንግዲህ አይኑረን' በሌላ አነጋገር፣ እራሷን እንደነፃነት መጠለያ የምትቆጥር አገር አንድ ስድስተኛው ሕዝቧ ባሪያ ሲሆን፣ አንድ አገር በጉልበት በሌላው ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ ሲደረግ፣ ብሎም ለወታደራዊ አገዛዝ ሲዳረግ እውነተኛ ሰዎች እምቢ ለማለት እና ለማመፅ ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል' ጉዳዩን የበለጠ አሣሣቢ የሚያደርገው ደግሞ አገራችን ተጠቂው ሣይሆን አጥቂው መሆኑ ነው'(11)
(9) ፓሌይ የተባሉት የእንግሊዝ ሥነ-መለኮት ምሁር በአብዛኛው የሞራል ጥያቄ አንቱ የተባሉ ሰው ናቸው፣ “መንግሥትን ስለመታዘዝ” በሚል ባስነበቡት ክፍል ማንኛውም ሃላፊነት የተገደበው በአዋጭነቱ ላይ ነው' በመቀጠልም እንዲህ ይላሉ* “ጠቅላላው ሕብረተ-ሠብ እስከፈለገው ድረስ፣ ማለትም በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት አለመታዘዝም ሆነ መለወጥ ሕብረተ-ሠቡን የሚጎዳ ከሆነ@ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት እንዲገዛ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው' በቃ፤ “---” በዚህ መርኅ ከተስማማን ዘንድ የማንኛውም አለመታዘዝ ፍትሐዊነት በአንድ በኩል የሚያስከትለው ጉዳትና አደጋ በሌላው ደግሞ ይህንን ለማከም የሚኖረውን ዕድል በማስላት እንደሚገደብ ነው'(12) ይህን በተመለከተ እንዲህ በማለት ይቀጥላሉ' እያንዳንዱ ሰው ለራሱ የሚዳኝ ይሆናል' ግን ሰውዬው የአዋጭነት ህግ የማይሰራባቸውን ጊዜያት የዘነጉ ይመስላሉ' ማለትም ሕዝብ እንደሕዝብ፣ ግለ-ሠብ እንደግለ-ሠብ፣ የሚከፈለው ዋጋ ምንም ያክል ከፍተኛ ቢሆን ፅድቅን ማድረግ ይገባዋል የሚለውን' አንድ ሰው ወደባህር እየሰጠመ ያላግባብ የሆነ ግንዲላ ብቀማው@ እራሴ መስጠም እንèን ቢያስፈልግ ሰጥሜ ያላግባብ የቀማሁትን የግድ ለባለቤቱ መመለስ አለብኝ' ግን እንደሳቸው ከሆነ ይህ አያዋጣም' ነገር ግን በእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል!”(13) እኝህ ሰዎች ባርነትንና ሌላውን አገር መውረር@ እንደሕዝብ ለመኖር እንèን ህልውናቸውን ጥያቄ ውስጥ ቢከትት@ የግድ ማቆም አለባቸው!
(10) በድርጊታቸው ሰዎች ከሌፓሌይ ጋር ይስማማሉ፣ ነገር ግን አሜሪካ ለአሁኑ አደጋ ተገቢውን ምላሽ ሰጥታለች ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆን?
“በብር የተንቆጠቆጠች* ሸርሙጣ፣
እንደፈጣን ሞተር መሾር ተክና፣
ፍለጋዋን በምናምንቴ ነገር ውስጥ ያ’ረገች*
‘ምሣለቃ ኮሚቴ¡” (14)
እንደ እውነቱ ከሆነ አሜሪካ ውስጥ ተሐድሦ እንዳይመጣ እንቅፋቶች በደቡብ ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖለቲከኞች ሣይሆኑ፤ እዚህ ያሉ ከሰው መብት ይልቅ ለንግድና ለእርሻ የበለጠ ፍላጎት ያላቸውና ለባሮችና ለሜክሲኮ፣ ምንም ያክል ዋጋ ቢያስከፍል ፅድቅን ለማድረግ ያልተዘጋጁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎች እና አርሦ-አደሮች ናቸው' በሩቅ ካሉ ጠላቶች ጋር ስጣላ አልገኝም' ነገር ግን እዚሁ ከኛ ጋር ሆነው ጨረታውን ከሚያካሂዱና ካለነሱ በቀር በሩቅ ያሉቱ ጉዳት ማድረስ ከማይችሉት ጋር ነው እንጅ' አብዛኛው ሰው አልተዘጋጀም የማለት ልምድ አለን፤ መሻሻል አዝጋሚ ነው፤ ምክንያቱም ጥቂቱ ከአብዛኛው ጠቢባን ወይንም የተሻሉ አይደሉም' ግን አብዛኛው እንዳንተ ጥሩ መሆን አይጠበቅባቸውም፣የሆነ ቦታ ፍፁም ጥሩነት መኖሩ አይቀሬ ነውና፤ “ያ ሊጡን ሁሉ ያቦካል'(15) በሀሳብ ደረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ባርነትንም ሆነ ጦርነቱን ይቃወማሉ፣ ሆኖም፣ ይህንን ለማቆም አንዳች እርምጃ አይወስዱም' የዋሺንግተንና የፍራንክሊን ልጆች በመሆናቸው ብቻ እየተኩራሩ፣ እጃቸውን ኪሣቸው ውስጥ ከትተው፣ ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም፣ ብለው ዝም ብለው ቁጭ ያሉ አሉ' እነዚህ የነፃነትን ጥያቄ ለነፃ ገበያ የሚያስተላልፉ ናቸው፣ ዝም ብለው የወቅቱን ዋጋ ከሜክሲኮ ከሚመጣው ሠበር-ምክር ጋር በማናበብ፣ ከእራት በçላ፣ ሊሆን እንደሚችለው፤ ሁለቱም ላይ ይተኛሉ' እንዲያው ለመሆኑ፣ የእውነተኛ ሰው ወይንም የኩሩ ዜጋ ያሁን ዋጋው ስንት ይገመት ይሆን? በተጨባጭ ምንም አያደርጉም፤ ነገር ግን ያቅማማሉ፣ ይቆጫሉ፣ አንዳንዴም በአክብሮት ጥያቄ ያቀርባሉ' ሌሎች ከቁጭት ይገላግሉዋቸው ዘንድ ይመኛሉ፤ እንዲህ ማሰብም ይቀናቸዋል' ቢበዛ ርካሽ ድምፃቸውን እና በጎ ምኞታቸውን ብቻ ያንፀባርቃሉ' ከአንድ ልባም ሰው ይልቅ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ በጎ አድራጊዎች ይኖራሉ' ነገር ግን ከአንድ ነገር ጊዜያዊ ጠባቂ ይልቅ ከባለቤቱ ጋር መደራደር ይመረጣል'
(11) ማንኛውም ምርጫ ቁማር እንደመቆመር ቢጤ ነው' እንደ ”ቼከር” እና እንደ ”ባክጋመን” ሁሉ ጥቂት ብቻ የሞራል ፍንጭ ያለበት፣ በእውነትና ውሸት መጫወት፤ እና ሁሌም የግድ ቁመራ ይከተለዋል' የመራጮች ስብዕና ስጋት አይሆንም' ምርጫዬን ስመርጥ፣ ምናልባት፣ እንደማስበው፤ ትክክለኛው ነገር እንዲፀና አጥብቄ አልኮነሰርም' ይህን ለአብላጫው ለመተው እፈቅዳለሁ' ስለዚህ ግዴታው ከአዋጭነት አያልፍም' ለትክክለኛው ነገር ድምፅ መስጠት እንèን ምንም ማድረግ አይደለም' ለሰዎች ልፍስፍስ በሆነ መንገድ ፍላጎቴን ማሳወቅ ነው' ጠቢብ ሰው ትክክለኛውን ነገር ለዕድልና ለአብላጫው ድምፅ አሣልፎ እንዲሰጥ አይፈቅድም' በአብላጫ ድምፅ ሊገኝ የሚችል በጣም ጥቂት መልካምነት ብቻ ነው' አብላጫው ባርነት እንዲወገድ ድምፅ የሚሰጠው አንድም በጉዳዩ ላይ ግድ ሲያጡ ሌላም በድምፃቸው ሊወገድ የሚችል ባርነት ሳይኖር ሊሆን ይችላል' ባርነትን ሊያስወግድ የሚችለው ነፃነቱን በድምፅ ማስረገጥ የሚችል ሰው ድምፅ ብቻ ነው'
(12) “በባልቲሞር”(16) ሊደረግ ስላለ ስምምነት እሰማለሁ' ወይም ሌላ ጋር ለፕሬዚደንት እጩነት የሚደረግ ምርጫ፣ በሙያቸው ፖለቲከኛ በሆኑ ሰዎች የተዋቀረ፤ ነገር ግን ለአንድ ነፃ፣ የገባውና አንቱ የተባለ ሰው ይኽ የሚደርሱበት ውሣኔ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም' ነገር ግን እኛ የእውነቱ ጥቅም ተካፋዮች መሆን አንችልም? ነፃ የሆኑ ድምፆችን መቁጠር አንችልም? በአገሪቱ ውስጥ ስምምነት ብቻ የሚያስተናግዱ አይኖሩ ይሆን? ነገር ግን አይደለም ኩሩ ዜጋ፣ ከአቋሙ መዋለልና፣ አገሪቱ ለርሱ ማዘን ሲገባት ለአገሩ ማዘኑ የማይቀር ይሆናል' ሳያመነታም፣ የቀረበውን ዕጩ እንደብቸኛ ተፎካካሪ በመውሰድ የሙሱናንን ዓላማ ያሳካል' ድምፁም የአንድ አቋም የሌለው መጤ ወይም ቅጥረኛ ባላገር ይሆናል' ባልንጀራዬ እንደሚለው ሰው ለሆነ ሰው ወዮለት! በጀርባው ውስጥ እጅ ማሣለፍ እንዳይቻል አፅም ለተገኘበት! ስታትስቲክሳችን ልክ አይደለም፣ የሰው ቁጥር ከልክ በላይ ተጋኗል' በአንድ ሺህ ካሬ ማይል ያለው ሕዝብ ምን ያክል ነው? በጭንቅ አንድ! አሜሪካ ሰዎች እንዲሰፍሩባት አንዳች ማበረታቻ አታደርግም? አሜሪካዊ ግራ ወደተጋባ ሰውነት ዝቅ ብሏል (17) በማኅበራዊ እሱነቱ ብቻ ከመታወቅ የማያልፍ የማስተዋልና በራስ የመተማመን ጉድለት የሚንፀባረቅበት፤ ወደዚህ ምድር ሲመጣ የመጀመሪያውና ዋንኛው ጭንቀቱ የመባ ቤቶች በጥሩ ጤንነት ላይ መሆናቸውንና፣ በሥርዓት አልባሌ እራፊ ከመልበሱ፣ ለሆኑ መበለቶችና አሣዳጊ ለሌላቸው ሕፃናት ገንዘብ ማሰባሰብ፣ ብሎም አጭር ዘመኑን በትኅትና ሊቀብረው ቃል በገባለት ኢንሹራንስ ኩባንያ ማህበር እየተረዳ መኖር ነው'
(13) ነገር ግን፣ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አንዱም ነገር፣ ግዙፉንም ጥፋት ቢሆን፣ ሌሎች ጉዳዮች ስለሚኖሩት ለማስወገድ ራሱን መስጠት የሰው ሃላፊነት መሆን አይኖርበትም' ሆኖም ቢያንስ እጆቹን መታጠብ ይኖርበታል፣ ሊያስበው ባይፈልግ እንèን ተጨባጭ ድጋፉን ሊሰጠው አይገባም' ሌሎች ፍለጋዎችንና ማሰላሰሎችን ለመከተል የወሰነኩ እንደሆነ፣ በቅድሚያ ከሌላው ትከሻ ላይ መውረዴንና እሱም የራሱን ፍለጋ እንዲከታተል መፍቀዴን ማረጋገጥ ይኖርብኛል' ያሣያችሁ! ምን ዓይነት ጅምላ ቅራኔ እንደተሸከምን* “ባሮችን ላለማሣደርና ወደ ሜክሲኮ ላለመሰለፍ እስቲ ትዕዛዝ ይውጣና፤ አላደርገው እንደሆነ እንተያይ!”፤ ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች አንድም በታማኝነታቸው* በቀጥታ፣ እንደዚሁም ጦርነቱን የጫረውን መንግሥት እምቢ ለማለት አቅም በሌላቸው ይጨበጨብላቸዋል፤ ልክ መንግሥት ለማሸበር የሚቀጥረውን እስኪቀጥር ድረስ ንስሐ ገብቶ ከደሙ የነፃና ለጊዜው ከኀጢአት ነፃ መሆን የሚችል ይመስል¡ ---፣ ከዚህም የተነሣ፣ በሥርዓትና በሰቪል መንግሥት ሥም፣ ሁላችንም ለክፋታችን ክፍያና ድጋፍ ለመስጠት እንገደዳለን' ከመጀመሪያዋ የግራ መጋባት ቸልተኝነት ኀጢአት፤ ከኢ-ሞራላዊ፣ እንደነበረው ላበጀነው ህይወት ፈፅሞ መከልከል እስከማንችል ሞራለ-ቢስ እንሆናለን'

ማስታወሻ*
1-  ከዋልዶ ኤመርሰን “ፖለቲካ”፣ 1844
2-  የአሜሪካና የሜክሲኮ ጦርነት (1846-1848)፣ ፀረ-ባርነቶች ባርነትን ወደቀድሞዋ ሜክሲኮ ማስፋፋት አድርገው ወስደውት ነበር'
3-  ከጠንካራ Æì የተሰራ፣ “ሕንድ” መባሉ ከምዕራብ ካሪቢያን የተገኘ መሆኑን ለማሣየት ነው'
4-  አብዛኞቹ ሥርዓተ-አልበኞች ከማሳሹሴይትስ የተነሱ መሆናቸውን ለመጠቆም ነው'
5-  ለወታደሮች የፈንጂ ዱቄት የሚዪዙ ልጆች'
6-  ቻርልስ ዎልፍ (1791-1823)
የሰር ዮሐንስ ሞር ቀብር ሥነ-ሥርዓት በኮሩና'
7-  ደንብ አስከባሪዎች'
8-  ሼክስፒር (1564-1616) የእንግሊዝ ፀሐፈ-ተውኔት፣ ከሐምሌት'
9-  ሼክስፒር፣ ከንጉስ ዮሐንስ'
10-  በ1775 በኮንኮርድና ሌክሲንግተን የተቀሰቀሰው የአሜሪካው አብዮት'
11- በአሜሪካ ያለውን ባርነትና የሜክሲኮን በአሜሪካ መወረር የሚያመለክት'
12- ዊሊያም ፓሌይ (1743-1805) የእንግሊዝ ሥነ-መለኮት ምሁርና ፈላስፋ፤ ከሞራልና ፖለቲካ ፍልስፍና መርኆች'
13- “ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል --- ”  ማቴዎስ 10፡39ሀ'
14- ሲሪል ቶርነር (1575?-1626) የበቃሉ ፍፃሜ'
15- “--- ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንዲያቦካ አታውቁምን”*
1ቆሮ5፡6'
16- በ1848፣ በዴሞክራቶች ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ታጭተው የነበሩት ሌዊስ በ|ላ በዘካሪያስ ቴለር የተሸነፉ'
17- ግራ የተጋቡ ሰዎች አባል፤ በመካከለኛው አስራሰባት መቶዎቹ በኒው ኢንግላንድ የተጀመረ ወንድማዊ ድርጅት'



አርማጌዶን ¡
(በተስፋዬ ቀኖ)
(Thoreau’s Essay On Civil Disobedience)
(ምዕራፍ ሁለት)

(1) ሠፊውና በብዛት የሚታየውን ስህተት ለማቆየት የባሰውን ሚዛናዊነት የጎደለው ክፋት ይጠይቃል' ጥቂቱ የጀግንነት መልካምነት የሚኮነንበት ሁናቴ ፃድቃን በአብዛኛው በራሣቸው ላይ የሚጋብዙት ነው' መንግሥት የሚፈፅመውን አድራጎት የሚኮንኑ፣ ግን ደግሞ ታማኝ የሆኑና ድጋፋቸውን የማይነፍጉት ያለምንም ጥርጥር አስተማማኝ ደጋፊዎቹና ለተሐድሦም እንቅፋቶች ናቸው' ከፊሉ መንግሥት ሕብረቱን እንዲያስቀር መንግሥትን ይማፀናል፣(1) የፕሬዚዳንቱን ጥያቄ ቸል እንዲባል' ለምን ራሳቸው አያስቀሩትም? ---፣ በነሱና በመንግሥት ያለው ሕብረት ---፣ እናም የድርሻቸውን በመንግሥት ካዝና አለመጨመር ነበረባቸው? ልክ እንደመንግሥት ያለ አቋም ላይ የሚገኙ አይደሉምን? ተመሣሣይ ምክንያቶች መንግሥት ሕብረቱን እምቢ እንዳይል አይከለክሉትም? እነሱ መንግሥትን እምቢ እንዳይሉ ያደረጉ ምክንያቶች አይደሉምን?
(2)ሰው እንዴት ግምትን ማስተናገድ ያረካዋል? ምኑ ያስደስተዋል? ግምቱ ተበደልኩ ከሆነ? በባልንጀራህ አንድ ዶላር እንèን የተታለልክ እንደሆነ፣ መታለልህን ካወቅክ ረክተህ አታርፍም፣ ወይም ተታልያለሁ በማለት  አታርፍም፣ ወይንም የሚገባህን እንዲከፍልህ በመጠየቅ አትረካም' ነገር ግን ተገቢውን እርምጃ ትወስዳለህ፤ ገንዘብህን ታስመልሳለህ፤ ዳግም እንዳትታለልም ትጠነቀቃለህ' ድርጊት ከመርኅ --- ትክክለኛውን ነገር መረዳት ብሎም መተግበር --- ነገሮችንና ግንኙነቶችን ይለውጣል፤ መንግሥትንና ቤተ-ክርስቲያንን ብቻ ሣይሆን፣ ቤተ-ሠብን ይካፋፍላል፤ አዎን! ግለ-ሠብን ይካፋፍላል፣ ሰይጣናዊውን ማንነት ከመለኮታዊው ማንነት ይለያል'
(3) ኢ-ፍትሐዊ ሕጎች አሉ፤ እነዚህን በመታዘዝ ልንረካ ነውን? ወይስ ለማስተካከል መጣር ይኖርብናል? እስኪቀናን ድረስ መታዘዝ ይኖርብን ይሆን? ወይንስ በአንድ ጊዜ እንተላለፋቸው?
ሰዎች በአብዛኛው በእንዲህ ዓይነቱ መንግሥት ሥር አብላጫውን የሕብረተ-ሠብ ክፍል  በማሣመን እስኪለውጡ መጠበቅ ያለባቸው ይመስላቸዋል' እምቢ ካሉ መፍትሔው ከችግሩ የባሰ እንዳይሆን ይፈራሉ' ግን ይህም ቢሆን የመንግሥት ጥፋት ነው፤ እራሱ እንዲባባስ ያደርገዋል' ለምን ተሐድሦ እንዲመጣ አይሰራም? ጥቂት ጠቢባኑን ለምን አያበረታታም? ከመነካቱ በፊት ለምን ያለቅሣል? ዜጎች ስህተቱን እንዲጠቁሙት ለምን አያበረታታም? የተሻለ ለመስራት ለምን አይጥርም? ክርስቶስን ሁልጊዜ ለምን ይሰቅላል? ኮፐርኒከስንና(2) ሉተርን(3) ለምን ያሣድዳል? ዋሺንግተንንና ፍራንክሊንን ለምን አመፀኞች ይላቸዋል?
(4) ማንም ሊያስብ እንደሚችለው ሆን ተብሎ በተጨባጭ ስልጣኑን አለመቀበል በመንግሥት ሊሰላሰል የማይችል ወንጀል ነው፤ ባይሆን፣ ትክክለኛውን፣ የሚጣጣመውን፣ ተገቢ ቅጣት ለምን አይሰጠውም? አንድ ንብረት-አልባ የሆነ ሰው ለመንግሥት ዘጠኝ ሽልንግ አላስገባ ቢል እኔ እስከማውቀው በማንኛውም ሕግ ላልተወሰነ ጊዜ እስር-ቤት እንዲቆይ ይደረጋል፣ በአሰሩትም ሰዎች በጎ-ፈቃድ የሚዳኝ ይሆናል፣ ነገር ግን ከመንግሥት ዘጠኝ ሽልንግ ቢሰርቅ እንደገና ወዲያው ይለቀቅልኛል¡
(5) ኢ-ፍትሐዊነት ለመንግሥት አስፈላጊው ሰበቃ ከሆነ፣ ይሁን! ይሁን! ማን ያውቃል እያደር ይስተካከል ይሆናል! --- በርግጥ መኪናው ያረጃል' ኢ-ፍትሐዊነቱ ምንጭ፣ እሽክርክሮሽ፣ ወይም ገመድ ለራሱ ያለው እንደሆን ፈውሱ ከክፋቱ ይብስ እንደሆነ ማየት ይኖRብን ይሆናል፤ ነገር ግን ተፈጥሮው ለሌላ ኢ-ፍትሐዊ ነገር የሚዳርገን ከሆነ፣ ሕጉን እንተላለፍ እላለሁ' ህይወታችን መኪናውን ለማቆም ተቃራኒ ሠበቃ ይሁን' እኔ ማየት የሚኖርብኝ፣ መቼም ቢሆን፣ የምኮንነውን ጥመት ስረዳ እንዳልገኝ ነው'
(6) መንግሥት ክፋትን ለመቀነስ ያስቀመጠውን መንገድ እንዳልከተል፣ እንዲህ ያለ መንገድ የማውቀው የለም' ረጅም ጊዜ የሚፈጅ ስለሆነ፣ የሰው ህይወት አስቀድሞ ያልፋል' ሌሎች ጉዳዮች አሉኝ' ወደዚህ ምድር በዋነኝነት የመጣሁት ይህን ምድር ለኑሮ የተመቸ ለማድረግ አይደለም' ነገር ግን፣ ጥሩም ሆነ መጥፎ በውስጡ ለመኖር ነው' ሰው ሁሉን ነገር ማድረግ አይጠበቅበትም፣ነገር ግን አንድ ነገር አለ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ስለማይችል አንድን ነገር ያላግባብ መፈፀም የለበትም' አገረ-ገዥውን፣ ተመራጩን መለመን በእነሱ ከመለመን ባለፈ፣ ሥራዬም አይደለም፣ ልመናዬን አልሰማ ካሉኝ፣ ምን ማድረግ አለብኝ? ግን በዚህ ላይ መንግሥት ያዘጋጀው ነገር የለም፤ የራሱ ሕገ- መንግሥት ክፉ ነው' ይህ በጣም ጨካኝ፣ አንገተ-ደንዳናና ዕርቅ-እምቢ ነው' ነገር ግን ሊያዝ የሚገባው ላቅ ባለ መልካምነትና ቁርጠኝነት ሊያደንቀውና በተገባው ብቸኛው መንፈስ ነው' ለመሻሻል የሚደረግ ለውጥ፣ ልክ እንደውልደትና እንደሞት ሰውነትን የሚያናውጥ ነው'
(7) ባርነትን የሚቃወሙ ሁሉ ባንድ ጊዜ ድጋፋቸውን፣ ባካልም ሆነ በንብረት ከአሜሪካን መንግሥት እንዲነፍጉ ጥሪ አቀርባለሁ' እና የአንድ የአብላጫ ድምፅ እስኪኖራቸው፣ ትክክለኛው ነገር በነሱ እስኪፈፀም፣ እንዳይጠብቁ እላለሁ' ሌላውን አንድ በመጠበቅ ፈንታ እግዚአብሔር ከእነሱ ጋር ከሆነ በቂaቸው ይመስለኛል' ከዚህም በላይ፣ ከባልንጀራው የበለጠ ትክክለኛ የሆነ ሰው አንድ አብላጫ እንደሆነ ይቆጠራል'
(8) ይህን ያሜሪካ መንግሥት፣ ወይንም ተወካዩን፣ ግዛቱን ፊት-ለፊት፣ በዓመት አንድ ጊዜ --- ብቻ --- በቀራጩ በኩል እገናኘዋለሁ'(4) ይህ በኔ ሁኔታ ያለ ሰው የሚገናኝበት ብቸኛው መንገድ ነው፤ ከዚያም እንዲህ ይለኛል፣ እወቀኝ፤ እና ቀላሉ፣ከሁሉ ኃይለኛና በተጨባጭ ባለው ሁኔታ፣ ካለሱ ሊኖር የማይቻል እንደሆነ በዚህ ጭንቅላት መቁጠር፣ ለራሱ ያለውን የወረደ እርካታ ወይንም ያለንን ፍቅር፣ አለመቀበል ግድ ነው' ባልንጀራዬ፤ ማለትም ቀራጩ ልፋረደው የሚገባ ሰው ነው' --- ምክንያቱም፣ ጥሌ ከሰዎች ጋር ነው እንጅ ከቁርበት ጋር አይደለም --- እና በምርጫው የመንግሥት ጉዳይ ፈፃሚ ሆኗል' ምንነቱን አሣምሮ የሚረዳበት መንገድና የመንግሥት ቅጥረኛ መሆኑን፣ ወይንም እንደ ሰው ነቱ፣ እኔን ባልንጀራውን እንደሚገባ ይመለከተኛል ይሆን ወይስ እንደ አክራሪ አድራጎቱን የሚመጥን ባልንጀርነታችንን የሚገታ የተጣደፈ ክፉ ቋንቋ፣ አስተሣሰብ፣ ሣያንፀባርቅ ያየኝ ይሆን? ይህንን አሣምሬ አውቃለሁ* እሱም አንድ ሺህ ሰዎች፣ አንድ መቶ ሰዎች፣ አስር ስማቸውን መጥቀስ የሚቻል ሰዎች --- አስር እውነተኛ ሰዎች ብቻ --- አዎን! አንድ እውነተኛ ሰው ብቻ፣ ባሮችን ላለማሣደር ቢቆርጥ፣ ካሣዳሪዎች ሕብረት ቢወጣና፣ በዚሁ ምክንያት ቢታሰር፣ ባርነት ካሜሪካ እንደሚወገድ እርግጠኛ ነኝ' ምክንያቱም ጅምሩ ጥቂት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን አንዴ እንደሚገባ የተከናወነ ለዘላለም ተከናወነ ማለት ነው' ግን የበለጠ ማውራቱ ይቀናናል' ተልዕኮአችን እንደሆነ እንናገራለን' ተሐድሦ ብዙ አገልጋይ ጋዜጦች አሏት፣ አንድም ሰው ግን የላትም' የኔ የተከበረው ባልንጀራዬ* የመንግሥት አምባሣደሩ(5) ጊዜውን በሙሉ በምክር-ቤት አዳራሽ ውስጥ የሠብዓዊ ጥያቄዎችን ሲያስተናግድ የሚውለው፣ በ”በካሮላይና” ግዛት እስር ቤቶች ከመደናገጥ ፈንታ የባርነት ኀጢአትዋን በእህትዋ ላይ ለመጫን በምትፈቅደው ማሳሹሴይትስ እስረኛ ለመሆን ተቀምÚል፣  --- ምንም እንèን ባሁኑ ሰዓት ከሷ ጋር የቅራኔ ቦታ ብትሆንም --- ግዛቷ ጉዳዩን ለሚቀጥለው በጋ እንዲስተላለፍ ታደርጋለች!
(9) አንድን ሰው ያላግባብ በሚያስር መንግሥት ሥር የፃድቅ ሰው ትክክለኛ ቦታም እዚያው እስር ቤት ነው' ትክክለኛው ቦታና አሜሪካ ለነፃና ለባለሙሉ ተስፋ መንፈሦች ያዘጋጀችው ቦታ በእስር-ቤቷ ነው' በዚያ ከመንግሥት ወጥተው በራሷ ሥራ እንዲጣሉና እንዲቆለፍባቸው፤ በመርኃቸው አስቀድመው ራሳቸውን እንደለዩት* ከባርነት የሸሹት፣ የሜክሲኮ የቁም እስረኞች እና ሕንዶች የዘራቸውን በደል የሚVገቱት ከዚያ ነው' በዚያ በተለየ ነፃና የተከበረ ቦታ፣ መንግሥት ከእሷ ጋር ያልሆኑትን፣ የሚቃረኗትን የምታጉርበት* በባሪያ መንግሥት ውስጥ ነፃ ሰው በክብር የሚኖርበት ሥፍራ! ማንም እዚያ በመወርወሩ ተፅዕኖው የሚቀንስ፣ ጩኸቱም ከእንግዲህ ወዲያ የመንግሥት ጆሮ የማያስጨንቅ፣ እንደቀደመውም በግድግዳዎቹ ውስጥ ጠላትነት የሚቀንስ ቢመስለው፤ እውነት ከውሸት የበለጠ እንዴት ኃይለኛ እንደሆነ  እንደሚገባ ባለማወቁ ብቻ ነው' ወይንም በራሱ ህይወት ፍትሐዊነትን የተለማመደ ሰው በተሻለና ውጤታማ በሆነ መንገድ ሃላፊነቱን በበለጠ ሊወጣ ይችላል' ብጣሽ ወረቀት ብቻ ሣይሆን ድምፅህን ስጥ፣ ሁለንተናህን ጨምር! አናሣ ከአብላጫ ጋር ተመሳስሎ ሲæዝ ጉልበት አይኖረውም' በዚያን ጊዜ ታዲያ አናሣ እንèን ሊባል አይገባውም' ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ደንቃራ ሲሆን የማይቋቋሙት ነው' ምርጫው ፃድቅ ሰዎችን በሙሉ እስር-ቤት ማጎር ወይንም ባርነትን ማቆም ከሆነ፤ መንግሥት ምርጫው የሚጠፋት አይደለችም' አንድ ሺህ ሰዎች ዘንድሮ ግብራቸውን ባይከፍሉ ያ ደም የሚያቃባ የኃይል እርምጃ አይሆንም' ይህም ግብሩን ከመክፈልና መንግሥት የንፁሃንን ደም እንድታፈስ ከመርዳት ጋር አይስተካከልም' እንደእውነቱ ከሆነ የሠላማዊ አብዮት ፍቺው ይኽ ነው፤ --- እንዲህ ዓይነት ነገር የሚቻል ከሆነ! 
ግብር ሰብሳቢው ወይንም ሌላ የመንግሥት ጉዳይ ፈፃሚ አንድ ጊዜ አንዱ እንደጠየቀኝ* “ምን ማድረግ አለብኝ?” “አንዳች ነገር ማድረግ ብትፈልግ ሥራህን ልቀቅ!” ጉዳይ-ፈፃሚው ታማኝነቱን እምቢ ሲልና ሥራውን ሲለቅ አብዮቱ ተከናወነ ማለት ነው' ነገር ግን ደም ሊፈስ ይገባዋል እንበል' ኅሊና ሲቆስል ደም ከቶ አይፈስ ይሆን? በዚህ ቁስል በኩል የሰው ሰውነቱ፣ እና ዘላለማዊነቱ ይፈሣሉ' እናም እስከ ዘላለማዊው ሞት ድረስ ይደማል' ይኽ ደም አሁን እየፈሰሰ ይታየኛል!
(10) የሕግ ተላላፊውን መታሠር፣ሁለቱም አንድ ጥቅም ያለቸው ቢሆንም፤ ከንብረቱ ቁጥጥር ሥር መዋል ይልቅ ደጋግሜ ለማሰላሰል ሞክሬአለሁ፤ ምክንያቱም ለእውነቱ የሚቆሙና ለነቀዘች መንግስት አደገኞች የሆኑቱ አብዛኛውን ጊዜ ንብረት በማፍራት የተጠመዱ አይደሉም' ለእንደዚህ ዓይነቶች መንግሥት አነስተኛ ግልጋሎት የምትሰጥ ይሆናል' በተለይ  በጉልበታቸውና በእጃቸው የሚያገኙት ከሆነ' ከገንዘብ ውጪ መኖር የቻለ ካለ መንግሥት ከርሱ አንዳች የምትጠብቅ አይደለም' ነገር ግን ሀብታሙ ሰው ሀብታም እንዲሆን ላደረገው ተቋም የተሸጠ ነው' ገንዘብ በዛ ማለት መልካምነት ቀነሰ ማለት ነው' ምክንያቱም ገንዘብ በሰውና በግቡ መሐከል ስለሚቆም ነው፤ እናም ለእርሱ a™X ያስገኝለታል' ሀብታም ባይሆን ለመመለስ ግብር የሚደረግባቸውን ብዙ ጥያቄዎች ፀጥ ያደርግለታል' የሚቀረው የመጨረሻው ጥያቄ ገንዘቡን እንዴት እንደሚያወጣው ይሆናል' ስለሆነም የሞራል መቆሚያው ከእግሩ ሥር ተወስዶበታል' የመኖር ዕድል ከማድረግ መንገዶች መጨመር አንፃር ይቀንሣል' አንድ ሰው ሀብታም ሲሆን ለራሱ ሕዝብ ማድረግ የሚችለው የተሻለ ነገር ድሃ በነበረ ዘመን ሲመኛቸው የነበረውን ነገሮች ለማድረግ መጣር ነው' ክርስቶስ ሄሮዳውያንን ባሉበት ሁኔታ እንዲህ አላቸው' “የግብሩን ብር አሣዩኝ” አለ* እነርሱም ዲናር አመጡለት' የቄሣር ምስል ያለበትን ገንዘብ ከተጠቀማችሁ፤ እርሱ ዋጋ የሰጠውንና ሥራ ላይ እንዲውል ያደረገውን ገንዘብ ከተጠቀማችሁ፤ ማለትም የመንግሥት ሰው ከሆናችሁ፤ እና የቄሣርን መንግሥት በደስታ የምታጣጥሙ ከሆናችሁ፤ ያኔ ጥያቄ ሲያቀርብ መልሣችሁ የራሱን ገንዘብ ስጡት፤ “እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው'”(6) በፊት ከነበሩበት ሁኔታ ባልተሻለ የትኛው የቱ እንደሆነ ማወቅ ስላልወደዱ ባሉበት ሁኔታ ተዋቸው'
(11) ነፃ ከሆኑ ባልንጀሮቼ ጋር ስነጋገር፤ ስለነገሩ ስፋትና አሣሣቢነት፤ እንዲሁም ለሕብረተ-ሠቡ መረጋጋት ያላቸውን ስሜት ለመረዳት ስሞክር፤ ነገሩ ሲጠቃለል እንደዚህ ነው' ያም ካለው መንግሥት ጥበቃ ውጭ መኖር እንደሚያሰጋቸው ነው' ይህም የመንግሥትን ጥያቄ እምቢ ካሉ በንብረታቸውና በቤተ-ሠባቸው ላይ የሚደርሰውን በማሰብ እየሰጉ እንደሆነ እገነዘባለሁ' በእኔ በኩል መንግሥት ጥበቃ ላይ መታመን እንደሚገባኝ ፈፅሞ አላስብም' ነገር ግን የግብር ጥያቄውን ሲያቀርብ እምቢ ያልኩት እንደሆነ ያለኝን ንብረት በሞላ ይወስDና ያበላሽብኛል' እናም እኔንና ልጆቼን እስከመጨረሻው ያዋክባል' ይህ ከባድ ነው' ይህ ማንም ለእውነት እንዳይኖር ያደርገዋል' በውጪም ሲታይ ተደላድሎ ለመኖር አዳጋች ያደርገዋል' በመሆኑም ንብረት ማከማቸት የሚመከር አይሆንም፤ ምክንያቱም ተመልሦ መሄዱ አይቀሬ ነው' ስለዚህ በልክ ጥቂት እርሻ አርሦ እና ጥቂት በልቶ መኖር ተገቢ ነው' እንዲሁም በራስ ህይወት ረክቶ መኖር እጅግ የተገባ ነው' በራስ ላይ መደገፍና መደላደል፤ ለእንደገና ጅማሬም ዝግጁ መሆን፤ በብዙ ጉዳይ አለመጠላለፍ ተገቢ ነው' ሰው በቱርክ እንèን ለቱርክ መንግሥት ራሱን ካስገዛ ሀብታም መሆን አያቅተውም' ኮንፊዩሸስ እንዲህ ብሏል፣ “መንግሥት ለምክንያታዊነት መርኅ ከተገዛ ድህነትና ሰቆቃ አሣፋሪ ናቸው፤(7) በአንፃሩ ለምክንያታዊነት መርኅ ካልተገዛ ሀብትና ክብር አሣፋሪ ናቸው” አይደለም! የአሜሪካ ጥበቃ በሩቅ ባሉት ነፃነቴ ጥያቄ ውስጥ በገባባቸው የደቡብ ክልሎቼ እስካልተደረገልኝ ድረስ፤ ወይንም እኔ እራሴን በሠላማዊ ሁኔታ ንብረት ማፍራት ላይ ካልገደብኩ በስተቀር ለአሜሪካ እምቢ ለማለት አይገደኝም፤ ንብረቴንም ሆነ ህይወቴን ባለመታዘዜ የምከፍለው ዋጋ ያነሰ ይሆናል' ያኔ እኔ የተሻለ ዋጋ እንዳለኝ ይሰማኛል'
(12) ከተወሰኑ ዓመታት በፊት እኔ ሣልሆን አባቴ ለሚገለገልባት ቤተ-ክርስቲያን ሠባኪ ለሆነ ግለ-ሠብ በቤተ-ክርስቲያን በኩል መንግሥት የተወሰነ ገንዘብ እንድከፍል አዛኝ ነበር' “ክፈል” አለች ”ካልሆነ እስር-ቤት ትወረወራለህ”፤ አይሆንም አልኩኝ' የሚያሳዝነው ሌላ ሰው ልክፈል አለ' እኔ ለምን አስተማሪው ለቄስ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚቀረጥ እና ቄሱ ለአስተማሪው ድጋፍ ለማድረግ እንደማይቀረጥ አይገባኝም' ምክንያቱም የመንግሥት ተቀጣሪ አስተማሪ አይደለሁም' በራሴ ፈቃድ ራሴን የደገፍኩ በመሆኔ ነው' እኔ ለምን አስተማሪው(8) የግብር ጥያቄውን ለመንግሥትና ለቤተ-ክርስቲያን ማቅረብ እንደማይችል ፈፅሞ አይገባኝም' ሆኖም ከላይ ለቀረበልኝ ጥያቄ እንደሚከተለው መልስ ሰጥቻለሁ' “ሰውን በተስጥዖው እንወቅ* እኔ ሄንሪ ሦሮ፣ ያልፈቀድኩት ማኅበር አባል ሆኜ መቆጠር አልፈቅድም” ለከተማው ፀሐፊ ይህንን ሰጠሁት፣ እናም ተቀበለኝ' መንግሥትም የዚያ ቤተ-ክርስቲያን አባል ሆኜ መቆጠር እንዳልወደድኩ ተገንዝባ፤ ከዚያ ወዲህ ተመሣሣይ ጥያቄ አቅርባልኝ አታውቅም' ዝርዝራቸውን ባውቅ ኖሮ ያልተመዘገብኩባቸው ማኅበራት ሁሉ እንዲያሰናብቱኝ ባረግኩ ነበር፤ ነገር ግን ዝርዝራቸውን ከወዴት አባቴ ላግኝ?
(13) የምርጫ ታክሱን ለስድስት ዓመታት አልከፈልኩም' በዚህም ምክንያት አንድ ጊዜ ላንድ ሌሊት ታስሬ ነበር' እና የቆምኩበትን አንድ ሜትር ያክል ውፍረት ያለው፣ የእንጨትና የብረት መዝጊያ ሳስተውል ወደእስር በጨመረኝ ተቋም ሞኝነት * ልክ ሥጋ፣ ደምና አጥንት ብቻ እንደሆንኩ ቆጥሮ እንዲቆለፍብኝ በማድረጉ ተደንቄአለሁ' እኔንም ሊያደርግ የሚችለው የመጨረሻው ነገር ይኽ እንደሆነ በደንብ አስቦበታል' ከዚህ የተሻለ ማሰብ አልሆነለትም' በእኔና በከተማዬ ሰዎች መሐል የድንጋይ ግድግዳ ቢኖር፤ ከዚህ የሚበልጥ ሊወጡትና ሊሰብሩት የሚገባ ግድግዳ እንዳለ ተረዳሁ' ያኔ እኔ እንደሆንኩት ነፃ መሆን ይችላሉ' አንዴም በምንም ሁኔታ ከምንም የተገደብኩ እንዳልሆንኩና፤ ግድግዳዎቹ የድንጋይና የሲሚንቶ ብክነት እንደሆኑ ተሰማኝ' ከከተማዬ ሰዎች እኔ ብቻ ግብሬን የከፈልኩ ሆኖ ተሰማኝ' በጥቅሉ እንዴት እንዲያረጉኝ በቅጡ አላወቁም' ልክ እንዳልተገሩ ዝርያዎች ሆኑብኝ፤ በማንኛውም መንገድና አንፃር የተሣሣተ ነገር አለ' ምክንያቱም ከግድግዳው ወዲያ መቆም የፈለግኩኝ መስሎአቸዋል' እንዴት በተንኮል በማሰላሰሌ ላይ ሊቆልፉ እንደሞከሩ ሣሥተውል አለመሣቅ አልቻልኩም' ሆኖም ማሰላሰሌ ልክ ወዲያው ያላንዳች መከልከል ተከትሎአቸው መውጣት አልተሣነውም' ለእነርሱ ይብላኝላቸው እንጅ! ሊደርሱብኝ እንዳይችሉ ሲረዱ አካሌን ሊቀጡ ቆረጡ' ልክ እንደ ሕፃናት፣ ሊያጠቁ ያልቻሉትን ሰው ውሻ እንደሚያስቆጡት' መንግሥት ግማሽ አስቂኝ፣ ብቻዋን እንዳለች፣ አንፀባራቂ ማንኪያ የያዘች ፈሪ ሴት እንደሆነች አየሁ' ዘመዶን ከጠላቶ መለየት የማትችል መሆኗን በማየት የቀረኝን ከበሬታ ሁሉ አVጥጬ እጅግ አዘንኩላት'
(14) ስለሆነም መንግሥት የሰውን ስሜት አስተሣሰብና ሞራል ሆን ብላ ፊት ለፊት መፋለም አትችልም' በተሻለ እውነተኝነትና ሚዛን የታጠቀች አይደለችም' ነገር ግን ብልጫዋ በጉልበት ብቻ ነው' እኔ ለጉልበት ለመንበርከክ አልተፈጠርኩም' የምተነፍሰው በራሴ መንገድ ነው' እስቲ ኃይለኛው ማን እንደሆነ እንተያይ' አዳሜ ጉልበቱ ምንድን ነው? እኔን ግድ ሊሉኝ የተገባቸው ከኔ ከፍ ላለ ሕግ የሚገዙ ብቻ ናቸው፤ እንደነርሱ እንድሆን ግድ ይሉኛል' ሰው በአዳሜ እንዲህና እንዲያ ሲገደድ አላውቅም' እንደዛ ዓይነቱ ምን ዓይነት ህይወት ይሆን? ከመንግሥት ጋር ስገናኝና* “ብርህን ወይንም ሕይወትህን” ስትለኝ ገንዘቤን ለመስጠት ለምን እቸኩላለሁ? ምንም ጥርጣሬ ሊገባችሁ አይገባም፤ እኔ እንደማደርገው አድርጉ፤ እኔ ለሕብረተ-ሠቡ መኪና እንደሚገባ መስራት የምጠየቅ አይደለሁም፤ የመሐንዲሱ ልጅ አይደለሁም' ሁለት ፍሬዎች ጎን ለጎን ሲወድቁ፣ አንዱ ለሌላው ሲል እንዳለ አይቆይም፤ ሁለቱም የየራሳቸውን ሕግ ይታዘዙና፤ እንደተቻላቸው አድገው ፍሬ ያፈራሉ፣ ይህም አንዱ ሌላውን በልጦ ሌላውን እስኪያጠፋው ድረስ ነው' ለተፈጥሮው ሊገዛ ካልቻለ ማንኛውም ተክል ይሞታል፤ ሰውም እንዲሁ!

    ማስታወሻ*
1-  “ከባሪያ ንግድ ጋር አንተባበርም!” የፀረ-ባርነት አራማጆች መፈክር ነበር'
2-  ኒኮላስ ኮፐርኒከስ (1473-1543)፣ ፖላንዳዊው የዘመናዊ ህዋው ተመራማሪ፤ በ1543 “የዓለማት ዑደት” የተሰኘውን ሥራውን ለጳውሎስ 3ኛ፣ የወቅቱ ሊቀ-ጳጳሳት አበርክቶ ማሣተሙንና፤ በዚሁ ምክንያት ከቤተ-ክርስቲያን መባረሩን ለማመልከት'
3-  ማርቲን ሉተር (1483-1546) የጀርመን መነኩሴና የፕሮስቴንታንት ተሐድሦ መሪ'
4-  ሳም ስታፕልስ፣ የኮንኮርድ ወረዳ ደንብ አስከባሪና ቀራጭ'
5-  ሳሙዔል ሆር (1778-1856)
ከኮንኮርድ በማሳሹሴይትስ ገዥዎች ወደ ደቡብ ካሮላይና የነፃ ጥቁር መርከበኞችን ቁጥጥር ስር መዋል ለመቃወም የተላከና፣ ሥራ ለመልቀቅ የተገደደ ሴት ልጁ ለኤመርሰን ቤተ-ሠብ የቅርብ æደኛ ከመሆኗም በላይ የሦሮ የልጅነት ædኛው ነበረች'
6-  ማቴዎስ 22፡19-22
7-  ዓናሌክትስ፣ 8፡13
8-  የሕዝብ ሌክቸር የሚካሔድበት አዳራሽ'


አርማጌዶን ¡
(በተስፋዬ ቀኖ)
(Thoreau’s Essay On Civil Disobedience)
(ምዕራፍ ሦስት)

(1) እስር-ቤት ያሣለፍኩት ሌሊት አስገራሚና አስደናቂ ነበር' እስረኞች እኔ ስገባ እየተጫወቱና የምሽቱን አየር በመግቢያው በር ሆነው እያጣጣሙ ነበር' ነገር ግን አሣሪው እንዲህ አለ* “ኑ ሰዎች ሰዓቱ ደረሰ!” እናም ሁሉም ተበተኑ፤ ቀጥሎም ወደ ደባቹ አፓርታማዎቻቸው መመለሣቸውን በኮቴአቸው ድምፅ ሰማሁ' የእኔ የክፍል æደኛ በአሣሪው ከኔጋ ተስተዋወቀ' በሩ ሲቆለፍ ባርኔጣዬን የምሰቅልበት ቦታ አሳየኝ፤ እንዲሁም ነገሮችን በእስር-ቤቱ ውስጥ እንዴት ሲያስተናግድ እንደከረመ አጫወተኝ' ክፍሎቹ በወር አንድ ጊዜ ኖራ ይቀባሉ' ይኽኛው ክፍል፤ ቢያንስ ካሉት ሁሉ ነጣ ያለው፣ በቀላሉ በተለያዩ ዕቃዎች የተሞላ፤ እና በከተማዋ ካሉት የፀዳው ነበር' ከየት እንደመጣሁና ወደዚህ ስፍራ ያመጣኝን ጉዳይ ለማወቅ ፈለገ፤ ታዲያ ሁሉን ከነገርኩት በ|ላ በተራዬ እንዴት ወደዚህ ስፍራ ሊመጣ እንደቻለ እውነተኛ ሰው ሊሆን እንደሚችል በመገመትና እንደተለመደውም በማመን ጠየቅኩት'“ግን ለምን?” አለ “ጎረኖ አቃጠልክ ይሉኛል፤ በፍፁም ያላረኩትን'” በ|ላ ልደርስበት እንደሞከርኩት በስካር መንፈስ ወደ ጎረኖ ገብቶ ሲጋራውን ሲለኩስ ቃጠሎው ተከስቶ ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ' ሁነኛ ሰው ስለመሆኑ የተመሰከረለት ሲሆን፤ በእስር-ቤቱ ውስጥ ለሦስት ወር ፍርዱን ሲጠባበቅ የቆየና ከዚያም በላይ ሊጠብቅ የሚችል ሰው ነበር' ነገር ግን በጣም የተገራና የረካ ሰው ነው፤ የሚተኛበትን ጣውላ በነፃ በማግኘቱ፣ በሚገባ እንደተያዘ ሆኖ ይሰማዋል'
(2) እሱ አንደኛውን መስኮት፤ እኔ ደግሞ ሌላኛውን ያዝን' አንድ ሰው በዚህ ስፍራ ረዘም ላለ ጊዜ ቢቆይ ዋነኛው ተግባሩ በመስኮት ወደውጪ መመልከት እንደሚሆን ገባኝ' ወዲያው እዚያ ያገኘኋቸውን ፅሑፎች አንብቤ የቀደሙት እስረኞች በየት በኩል እስር-ቤቱን ሰብረው እንዳመለጡ ሁሉ አነበብኩ፤ እንዲሁም የእሣት ማንደጃውን ሥፍራና በክፍሉ ቀድመው የነበሩ እስረኞች አከራረም ምን እንደሚመስል ተረዳሁ' እዚህ ከእስር-ቤቱ ግድግዳዎች አልፈው የማይሄዱ ታሪኮችና አሉባልታዎቸ ማግኘት ችያለሁ' ይመስለኛል* በከተማችን ውስጥ ቅኔ የሚቋጠርበትና ተፅፎ በሰርኩላር መልክ ላይታተም የሚዘጋጅበት ቦታ ነበር' ከእስር-ቤቱ ለመጥፋት ሲሞክሩ የተደረሰባቸው ወጣቶች በጣም ረጅም የሆኑ የቅኔ ስንኞች ዝርዝር አዘጋጅተው የተመለከትኩ ሲሆን፣ገጠመኛቸውን የቋጠሩትን ቅኔ በመዘመር ግፍን እንደሚበቀሉም አስተውያለሁ'
(3) አብሮን የታሰረውን ወዳጄን ዳግም ላላገኘው እችላለሁ በሚል ፍራቻ የምችለውን ያክል ካዋራሁት በ|ላ አልጋዬ የት እንደሆነ አሣይቶኝ መብራቱን ሊያጠፋ ተለየኝ'
(4) በእውነቱ ለመናገር ከሆነ ክስተቱ ወደሩቅ አገር ከሚደረግ ጉዞ ጋር ይመሳሰል ነበር' ያውም ፈፅሞ ዐይኔ ያያል ብዬ ያልገመትኩት ክስተት' በዚህ ስፍራ ለአንድ ቀን ማደር፣ ከዚያ በፊት ሰምቼ የማላውቀውን ያክል የከተማው ሰዓት ሲያቃጭል መስማት፤ በአጠቃላይ የመንደሩ የሌሊት ድምፅ፤ ምክንያቱም የተኛነው መስኮቶች ሣይዘጉ ነበር' የምኖርባትን መንደር በመካከለኛው ዘመን ዐይን እንደማየት ነበር' ኮንኮርድም ወደ ራይን ወንዝነት ተቀየረች' የፈረሶችና የሠረገሎች ሥዕል በፊቴ ተመላለሰ' በጎዳናዎች የሚሰማው የሽማግሌ መንደርተኞች ድምፅ ነው' ያለፍቃዴ ከጎናችን ባለው መሸታ-ቤት ኩሽና የሚደረገውንና የሚባለውን ነገር መስማትና መቆጣጠር ነበረብኝ' ፈፅሞ አዲስና በሕይወቴ እፁብ-ድንቅ ገጠመኝ ነበር' የምኖርባትን ከተማ በቅርበት ለመረዳት አስችሎኛል' እንደነገሩ ውስጥዋ ነበርኩኝ' ነገር ግን ተቋሞቿን ከዚህ ቀደም አላጤንèቸውም ነበር' ይኽ ከዓይነተኛ ተቋሞ አንዱ ነበር' ምክንያቱም የከተማችን ቁንጮ(1) በመሆኑ ነው' ነዋሪዎም እንዴት እንደሆኑ ለመረዳት ጀመርኩ'
(5) በማግስቱ ቁርስ በመዝጊያው ስር ባለ ቀዳዳ በኩል ቀረበልን' ቼኮላታ፣ ቡኒ ዳቦ፣ እና የብረት ማንኪያ በአነስተኛ አራት ማዕዘን ብረት ድስት ቀረበልን' ዕቃዎቹን እንድንመልስ ዳግም ሲጠሩን፤ የተረፈኝን ዳቦ ለመመለስ አስቤ ነበር፤ ነገር ግን æዴ ወዲያው ከለከለኝ፤ ለምሣና ለእራት ማስቀመጥ እንዳለብኝ ነገረኝ' ወዲያውም ቀጥሎ ያለውን ማሳ ሁሌም እንደሚያደርገው ሊኮተኩት ወጣ፤ እስከ ምሣም አልተመለሰም' ከዚያ በኋላ ሊያየኝ መቻሉን እየተጠራጠረ በሠላም ዋል አለኝ'
(6) አንድ ሰው ጣልቃ ገብቶ ግብሩን በመክፈሉ በማግሥቱ ከእስር-ቤት ስወጣ፣ ብዙ ለውጥ አልጠበቅኩም' ማለት በወጣትነቱ ታስሮ አርጅቶ እንደወጣ ሰው ዓይነት ማለቴ ነው' ነገር ግን በዐይኖቼ ፊት የዞረ ትርዒት ነበር' ከተማው፣ መንግሥትና ሕዝቡ* ጊዜ መለወጥ ከሚችለው በላይ በተለይም የምኖርበትን መንግሥት በጥሞና ለማጤን ሞከርኩ' አብሬአቸው የኖርèቸው ሰዎች ምን ያክል እንደ ጥሩ æደኛና እንደጥሩ ባልንጀራ ሊታዩ እንደሚችሉም አሰላሰልኩ' æደኝነታቸው ለተመቸው የበጋ ወራት ብቻ እንደሚያገለግል መንገድ ያክል ብቻ ሆኖ ተሰማኝ፤ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ የተዘጋጁ አይደሉም' በአድሏቸውና ምክንያታዊ ባልሆኑ እምነቶቻቸው ልክ እንደቻይናና እንደማሌዢያ ሰዎች ያክል ከኔ የራቁ ዝርያዎች እንደሆኑ ተሰማኝ' ለሰው ልጅ መስዋዕትነትን በመክፈል፤ አንድም አደጋ ለመቀበል የተዘጋጁ አይደሉም፤ ቢያንስ ንብረታቸውን እንèን ቢሆን፤ በአጠቃላይ የሚደነቁ ሰዎች አይደሉም' ነገር ግን የሰረቃቸውን መልሰው የሚሰርቁት ሆነው ታዩኝ' እናም የተወሰኑ ሥርዓቶችን በመፈፀምና ፀሎት በማድረግ እንዲሁም በአንድ ከንቱ ቀጥተኛ ግን ደግሞ ፋይዳ የሌለው መንገድ ከጊዜ ወደጊዜ በመæዝ ነፍሳቸውን ለማዳን ተስፋ የሚያደርጉ ምስኪኖች ናቸው' ይኽ ባልንጀሮቼን ጠንከር አድርጎ መዳኘት ሊሆን ይችላል'  ነገር ግን እንደ እውነቱ ለመናገር ከሆነ እስር-ቤቱን የመሰለ ተቋም በመንደሩ ውስጥ ስለመኖሩ እንèን አንዳች የሚያውቁት ነገር አልነበረም'
(7) በቀደሙት ጊዜያት በመንደራችን አንድ ልማድ ነበረ፤ አንድ ድሃ ባለዕዳ ከእስር-ቤት ሲለቀቅ የሚቀርቡት ሰዎች ሠላምታ ይሰጡታል' ይኽም የእስር-ቤቱ የእሳት ማንደጃ ክፍል መስኮት በጣቶቹ ላይ የሚያኖረውን ምልክት በማየት* “እንዴት ነው ታዲያስ?” ይሉታል' ለኔ ግን ባልንጀሮቼ ሠላምታ አላቀረቡልኝም' ነገር ግን አስቀድመው ወደኔ ተመለከቱ፤ ከዚያም እርስ በርሳቸው፤ ልክ ከሩቅ ጉዞ የተመለስኩ ተዥ ይመስል' ልክ የተበላሸ ጫማ፣ ጫማ ሰሪ ቤት ተወስዶ እንደሚሰራው እኔም እስር-ቤት ውስጥ ተወረወርኩ በሚቀጥለው ቀን ስወጣ ጉዞዬን ጨርሼ፣ ስለሌሎች መዝ ያለብኝን መንገድ ተጉዤ፣ ማስተላለፍ ያለብኝን መልዕክት ፈፅሜና የተጠገኑ ጫማዎቼን ተጫምቼ፤ ፈረሱ ተሰክሎ ነበርና፤ ጊዜ ሣላባክን ሦሥት ኪ.ሜ ያህል ራቅና ከፍ ብለው ካሉት ኮረብቶች ላይ ከሜዳው መሐል ተገኘሁ፤ ከዚያም ወዲያ መንግሥት ብሎ ተዓብ የትም አልታየም!
(8) ይህ “የእስሬ” ጠቅላላ ታሪክ ነው'(2)

                                   -------------------------------------

(9) የአውራ-ጎዳናውን ግብር ለመክፈል አላቅማማሁም' ምክንያቱም መጥፎ አገልጋይ የሆንኩትን ያክል ጥሩ ባልንጀራ ሆኜ መገኘት ስለነበረብኝ ነው' እንደዚሁም ትምህርት-ቤቶችን መደገፍን በተመለከተ ወገኖቼን ለማስተማር ድርሻዬን እየተወጣሁ ነው' ግብር አልከፍል ያልኩት ለተወሰኑ ነገሮች ብቻ አይደለም' ነገር ግን እኔ ያረግኩት ለመንግሥት ታማኝ ሆኜ ላለመገኘት እምቢ ብያለሁ' ይህም ከመንግሥት ጋር ላለመተባበርና ተነጥዬ ለመቆም ስል ነው' የእኔ ዶላር መጨረሻ ምን እንደሚሆን ማወቅ አላስፈለገኝም' እኔ ብፈልግ* ሰውን ተኩሶ መግደል ወይንም ጠብ-መንጃ ለመግዛት ወደ|ላ የሚል አይደለም* ዶላር የሚያውቀው ነገር የለም' ኀጢአት ሲያልፍም አይነካው' ነገር ግን የሚያስጨንቀኝ የታማኝነት ውጤት ነው' እንደ እውነቱ ከሆነ ከመንግሥት ጋር በእራሴ መንገድ፣ ጦርነት ማወጄ ነበር፤ ብዙውን ጊዜ በእንደዚህ ያሉ ጊዜያት እንደሚሆነው፣ ጨከን በማለት --- * ከሷ ላገኝ የምችለው ጥቅምም ሆነ ነገር ከኖረ'
(10) ሌሎች እኔ መክፈል የሚገባኝን ግብር ለመንግሥት ከመራራት ከከፈሉ፤ በራሳቸው እንዳደረጉት ማድረጋቸው ነው፤ ወይንም ከመንግሥት በበለጠ ኢ-ፍትሐዊነትን መርዳታቸው ሊሆን ይችላል' ግብሩን ለግለ-ሠቡ ካላቸው የተሣሣተ ፍላጎት፣ ንብረቱን ለማዳን፣ ወደ እስር-ቤት እንዳይወርድ፣ ከከፈሉ፤ የራሳቸው ስሜት በሕዝቡ ጥቅም ላይ የሚኖረውን ጫና ምን እንደሆነ በጥንቃቄ ስላልተረዱ ነው'
(11) ስለዚህ፣ በአሁኑ ሰዓት ያለኝ አቋም ይኽ ነው' ነገር ግን በእንደዚህ ያለ ጊዜ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል' ካልሆነ የምንወስደው እርምጃ ድርቅ ያለና በሰዎች ግምት ላይ በመመርኮዝ ትክክል ያልሆነ እርምጃ ሊሆን ይችላል' ስለዚህ በእንዲህ ያለ ጊዜ የሚመለከተውንና ጊዜው የሚፈልገውን ብቻ እናድርግ'
(12) እንዴት እንደሆነ ቢያወቁ፤ ባልንጀራን እንደዚህ ላለው ከባድ ያልተፈለገ አድራጎት መዳረግ ለምን አስፈለገ? ነገር ግን፣ ይመስለኛል* እነሱ እንደሚያደርጉት ለማድረግ ይኽ በቂ ምክንያት አይደለም፤ ወይንም ሌሎች የባሰ ሌላ ከባድ ነገር እንዲያደርጉ መፍቀድ' እንደገና፣ አንዳንድ ጊዜ ለራሴ እንዲህ እላለሁ፦ ብዙ ሚሊዮን ሰው፣ ያለሙቀት፣ ያለ ክፉ ሀሣብ፣ ያላንዳች ግላዊ ስሜት፣ ጥቂት ሽልንግ ሲጠየቁ፣ አወቃቀራቸው እንዲህ ስለሆነ፣ ይህንን ጥያቄአቸውን ማስቀየር ላይቻል፣ ብዙ ሚሊዮኖችን ለመቀየር በአንተ በኩል ምንም ዕድል ሣይኖርህ፣ ለዚህ ለአውሬ ጉልበት ለምን ራስህን ማጋለጥ አስፈለገ? ብርድና ረሃብን ንፋስንና ማዕበልንም ቢሆን እምቢ ማለት አትችልም፤ ለተመሣሣይ ሺህ ግዴታዎች ዝም ብለህ እሽ ማለት አለብህ፤ እራስህን እሳት ውስጥ እንደማትጨምረው ማለት ነው' ሆኖም ይኽ የአውሬ ጉልበት አይመስለኝም፤ ግን በከፊል ሰው-ሰራሽ ነው' ስለዚህም በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያለኝ ይመስለኛል' እነዚህም እንደ አውሬ ሊቆጠሩ አይችሉም' ስለዚህ ጥያቄው አግባብ ያለው ነው' በመጀመሪያ ከነርሱ በቀጥታ ለፈጠራቸው፤ ቀጥሎም ከራሳቸው ወደራሳቸው' ነገር ግን እራሴን እሣት ውስጥ ብጨምር እሣትም ሆነ እሣቱን የፈጠረውም ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም፤ መኮነን የሚገባኝ እራሴን ብቻ ነው' እራሴን ሰዎች ባሉበት ሁኔታ ለመርካት እራሴን ካሣመንኩ ማለትም ከነሱ የምጠብቀውና እራሴ መሆን የሚገባኝ ግንዛቤ ውስጥ ካልገባ* ልክ እንደ የዋሁ- መደዴ(3) እና አቦ-ሠጡኝ ነገሮች ባሉበት ሁኔታ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብዬ መርካት ይኖርብኛል፤ ከዚያም በላይ ይህንን እምቢ ማለትና የአውሬ ከሆነ ኃይል ጋር መጋጠም መሐከል ልዩነት አለ፤ ይህንን በተወሰነ ደረጃ መቋቋም ይቻላል፤ ነገር ግን እንደ ዖርፊዮስ(4) የድንጋይን፣ የዛፍንና የአራዊትን ባህርይ መለወጥ አይዳዳኝም'
(13) ከአንድም ሰው ጋር ወይም ሕዝብ ጋር መጣላት አልሻም፤ ፀጉር ለመሰንጠቅም አልፈልግም፣ ጥቃቅን ነገሮችን ለማጋነንም አልቃጣም፤ ከባልንጀሮቼም የተሻለኩ አድርጌ እራሴን ስቆጥር አልገኝም' ነገር ግን ከምድሪቱ ሕግ ጋር የምመሣሰልበትን ሰበብ አገኝ እንደሆነ እሞክራለሁ' ለዚህም ለመመሣሰል እጅግ ተዘጋጅቻለሁ' በእርግጥ እራሴን ለመጠራጠር ምክንያት አለኝ' በያመቱ ቀራጭ ወዳለሁበት አካባቢ ሲመጣ መንግሥትና ሕዝቡ የሚኖራቸውን ነገር ለማወቅ እጥራለሁ፤ ይህም ድንገት ለመመሣሰል የሚሆን ሰበብ ባገኝ ብዬ ነው'                 
“በአገራችን ላይ እንደቤተ-ሠባችን ሁሉ ተፅዕኖ ልንፈጥር
ይገባል፣
እና በማንኛውም ጊዜ ይህንን ለማክበር ያለንን
ፍቅር ወይንም ኢንዱስትሪ መነጠል ቢያስፈልግ፤
ነፍሳችንን ማስተማር የሚገባን፣
የኅሊናን እና የሀይማኖትን ነገር እንጅ
የደንብና የጥቅም መሻትን ነገር አይደለም'”(5)                       
(14) መንግሥት በዚህ ሁኔታ እጄ ውስጥ ያለውን ሥራ ሁሉ በአንድ ጊዜ ከእጄ ሊወስድ እንደሚችል አምናለሁ' ስለሆነም ከአገሬ ሰዎች የተሻልኩ አርበኛ መሆን አልችልም'
ዝቅ ካለ ቦታ ሲታይ ሕገ-መንግሥቱ ከነ ስህተቱ  በጣም መልካም ነገር ነው' ሕግና ፍርድ-ቤቶች በጣም ክብር የተገባቸው ናቸው፤ ይኽ ግዛትና የአሜሪካ መንግሥት በብዙ አቅጣጫ በጣም የሚደነቁና ምሥጋና የተገባቸው የማይገኙ ነገሮች ናቸው፦ ብዙዎች እንደመሰከሩላቸው' ግን ትንሽ ከፍ ተብሎ ሲታይ ከላይ እንደገለፅኩት ናቸው፤ ከዚያም በላይ ከፍ ተብሎ ሲታዩ ግን ማን እንዲህ ናቸው ሊል ይችላል? ለመታየት እና ለመታሰብ የተገባቸው መሆኑ ራሱ አጠያያቂ ነው'
(15) ነገር ግን የመንግሥት ነገር እኔን አያስጨንቀኝም፤ በጣም ጥቂቱን ሀሳቤን ብቻ ብሰጠው ይበቃል' በዚህም ዓለም እንèን ቢሆን በመንግሥት ሥር የምኖርባቸው ጊዜያት በጣም ጥቂት ናቸው' ሰው በአስተሳሰቡ ነፃ፣ ከተወሳሰበ ነገር ነፃ፤ ምናቡ ነፃ የሆነ እንደሆነ ለረጅም ጊዜ እንደማይመስለው፣ ጥበብ የጎደላቸው ገዥዎችና የተሐድሦ ሰዎች አደገኛ በሆነ መንገድ አያደናቅፉትም'
(16) አብዛኛው ሰው ከኔ በተለየ መንገድ እንደሚያስብ እረዳለሁ' ነገር ግን እንደ አሸን በፈሉ ሙያዎች የተጠመዱና በዚህ የሚኖሩ፤ በጥቂቱ ይስቡኛል' የመንግሥት ሰዎችና ሕግ አውጪዎች ሙሉ በሙሉ ተቋሙ ውስጥ ስለሚገኙ እውነቱ ተራቁቶና ተለይቶ አይታያቸውም' እነሱ ስለሚንቀሳቀሰው ሕብረተ-ሠብ ብቻ ያወራሉ፤ ያለእርሱ ግን ማረፊያ የላቸውም' የተወሰነ የልምድና የአድልዎ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ' ያለምንም ጥርጥር ብልህና እንዲያውም ጠቃሚ ሥርዓቶችን የፈጠሩ ናቸው' ስለዚህም ልናመሰግናቸው ይገባል' ነገር ግን ብልህነታቸውም ሆነ ጠቀሜታቸው አድማሱ የጠበበ ነው' ይኽ ዓለም ለፖሊሢና ለአዋጭነት ብቻ እንደማይገዛ ለአፍታም ቢሆን ሊዘነጉት አይገባም' ዌብስተር ከመንግሥት በኋላ ስለሚሄድ አፉን ሞልቶ በስልጣን ሰለመንግሥት ሊናገር አይችልም' የእርሱ ቃላት ጥበብነቱ ምንም መሰረታዊ ተሐድሦ ያለው መንግሥት ለማምጣት ለማያስቡ የሕግ አውጪዎች ብቻ ነው' ነገር ግን ለሚያሰቡና ለዘላለም ሕግ ለሚያወጡ፤ አንዴም ቢሆን ጉዳዩን ለማየት አይፈቅድም' እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ የመላምት ጥበበኞች በአንድ ጊዜ የአስተሳሰቡን አድማስና ተወዳጅነት ማሳየት እንዲችሉ አውቃለሁ' ሆኖም ከርካሽ የአብዛኛዎቹ የተሐድሦ ሰዎች ሙያ ጋር ሲነፃፀር፤ እንዲሁም በጠቅላላው የበለጠ ርካሽ ከሆነው የተናጋሪዎችና የፖለቲከኞች ጥበብ ጋር ሲነፃፀር የርሱ ትርጉም ያላቸውና ጠቃሚ ቃላት ናቸው' ስለዚህም ለአርያም ምስጋና ይግባው' ከሌሎች ጋር ሲወዳደር እርሱ ሁልጊዜ ጠንካራ ነው፤ ኦሪጅናል ነው፤ የተግባር ሰው ነው' ሆኖም ብቃቱ ጥበብ አይደለም፤ ነገር ግን ጥንቃቄ ነው' የሕግ ሰዎች እውነት እውነት አይደለም፤ ነገር ግን የተጣጣመ አዋጭነት ብቻ ነው' እውነት ከእራሷ ጋር የታረቀች ናት፤ እና የውሸትን እውነተኛ መሆን ለማሣየት በዋነኝነት የተኮነሰረች አይደለችም' የሕገ-መንግሥቱ ጠበቃ እንደተባለው ሊባል የተገባ ነው' በእርሱ ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ቡጢዎች አይኖሩም፤ ከመከላከል በስተቀር' የእርሱ መሪዎች የ”87” ሰዎች ናቸው(6) “ምንም ጥረት አላረግኩም” ይላል “ምንም ጥረት ለማድረግ ሀሣብ አልሰጠሁም፤ ምንም ጥረት አልተመለከትኩም፤ ለመመልከትም አልጣርኩም ግዛቶችን ወደ ሕብረት ለማምጣት በመጀመሪያ የተደረገውን ሥርዓት ላለመጋፋት ስል”' ሕገ-መንግሥቱ ባርነትን በተመለከተ አይቶ እንዳላየ ሲሆን አይቶ እንዲህ ይላል' “በመጀመሪያ የተደነገገው ማዕቀፍ አካል ስለሆነ ይፅና'(7) ምንም እንèን የተለየ ችሎታና ብልህነት ቢኖረውም ነገርን ከፖለቲካ ግንኙነቱ ነጥሎ በአእምሮው እንደሚገባ ማየት አይችልም' ለምሳሌ ባርነትን በተመለከተ በዛሬዋ አሜሪካ ያለውን ሁኔታ መንስዔ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን በሚመስል ግራ የተጋባ መንገድ ሊመልስ ይዳዳል፦ እንደ አንድ ግለሰብና በፍፁም አንድም አዲስና ብቸኛ የማኅበራዊ ሃላፊነት ላይ ሊደርስ ይችል ይሆን? “ነገሩ” ይላል እርሱ “የግዛቶቹ በባርነት የመገዛት ሚስጢር ለራሣቸው እንዲመች፤ በራሳቸው ተዋፅዖ ሃላፊነት እንዲኖራቸውና በጠቅላላው በንብረት፣ በሰው፣ በፍትሕና በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት ለመቆጣጠር እንዲቻል ነው' በተረፈ ከዚህ ውጭ ከሰብዓዊነት ወይንም ሌላ በመነጨ የሚፈጠሩ ማኅበሮች፤ ከዚህ ጋር ምንም የሚያያዝ ምክንያትነት የላቸውም' ስለሆነም ከኔ ምንም መበረታታት አግኝተው አያውቁም፤ ለወደፊቱም አያገኙም'
(17) እውነት የሚቀዳበትን የተሻለ ምንጭ የማያውቁ ከዛ ያለፈ መፍለቂያ እንዳለው ያልተረዱ በመፅሐፍ-ቅዱስና በሕገ-መንግሥቱ ተገድበው፤ በጥበብ ተገድበው፤ በመንቀጥቀጥና በትህትና ከዚያ ይጠጣሉ፤ ነገር ግን ወደዚህ ሐይቅ ወይንም ባሕር ቀስ ብሎ ሲንጠባጠብ የሚያስተውሉ፤ ወገባቸውን እንደገና አንድ ጊዜ ታጥቀው ወደ ምንጩ መፍለቂያ ጉዟቸውን ያቀናሉ'
(18) አንድም ሕግን ለማውጣት የሚበቃ ሰው በአሜሪካ አልተከሰተም' በዓለም ታሪክ ውድ ናቸው' እውነት ነው* ተናጋሪዎች፣ ፖለቲከኞች እና ያማረ ቋንቋ ባለቤቶች በሺዎች ይገኛሉ' ነገር ግን የዛሬውን አስጨናቂ ጥያቄ ሊመልስ የሚችለው ተናጋሪ ግን እስካሁን አፉን አልከፈተም' ያማረን ቋንቋ ለራሱ ስንል ብቻ እንወደዋለን እንጅ አንዳች እውነት ስለሚገኝበት ወይንም አንዳች ጀግንነት ስለሚያነቃቃ አይደለም'
ሕግ-አውጪዎቻችን እስካሁን ለአገራችን ነፃ ንግድና ነፃነት፣ ሕብረት፣ እና ፅድቅ ያለውን ተነፃፃሪ ዋጋ ገና አልተረዱም' ዝቅ ላሉት የግብር እና የፋይናንስ፣ የንግድ የፋብሪካና፣ የግብርና ጥያቄዎች ማሰብ የሚችል  አዕምሮ የላቸውም' በምክር-ቤት ላሉ ሕግ-አውጪዎች ቀልድ ምሪት ብቻ እራሳችንን ችላ ካልንና በሕዝቡ ተጨባጭ ቅሬታዎች ካልተስተካከልን በስተቀር፤ አሜሪካ በአሁኑ ሰዓት ያላትን ደረጃ በአገራት ዘንድ በቀጣይነት ሊኖራት አይችልም' ለአስራ ስምንት መቶ ዓመታት፤ እንድል ከተፈቀደልኝ፤ አዲስ-ኪዳን ከተፃፈ ጀምሮ በሕግ-ቀረፃ ሣይንስ ላይ ሊፈነጥቅ ያለውን ብርሃን ለማስተናገድ ጥበብና የሞራል ብቃት ያለው የሕግ-አውጪ የትኛው ይሆን?
(19) ልገዛለት ፈቃደኛ እና ደስተኛ የምሆንለት መንግሥት* ከኔ የተሻለ ለሚሰሩና ለሚያውቁ ለመታዘዝ ደስተኛ እንደመሆኔ መጠን* አብዛኛውን ጊዜ ግን የተሻለ የማያውቁና የማያደርጉ፤ እስካሁን ያልፀዳ ነገር ነው' የምር ፍትሐዊ ለመሆን የተገዢውን ፈቃድና ስምምነት ሊኖረው ይገባል' እኔ ፈቅጄ ከምስማማበት ነገር በቀር በእኔ ማንነት እና ንብረት ላይ አንዳች መብት ሊኖረው አይገባም' ከፍፁም ንጉሣዊ አገዛዝ ወደ ከፊል ንጉሣዊ አገዛዝ፤ ከከፊል ንጉሣዊ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገው ዕድገት፤ ለግለ-ሠብ አክብሮት የመስጠት ትክክለኛ ዕድገት ነው' የቻይናው ፈላስፋ እንèን ሣይቀር ግለ-ሠብ ለአገር መሠረት መሆኑን ለመረዳት ጥበብ አልጎደለውም'(8) ለመሆኑ ይህ የምናየው ዴሞክራሲ ለመንግሥት የመጨረሻው መሻሻል ይሆን? ለዜጎች መብት እውቅና መስጠትና ማቀናጀት አይቻል ይሆን? 
መንግሥት ግለ-ሠብን  እንደ የበላይ እና እራሱን የቻለ ኀይል መቁጠር እስካልቻለ ድረስ፣ አንድ መንግሥት በእውነት ነፃና የበራለት መንግሥት መሆን አይቻለውም' የእራሱ ጉልበትና ሥልጣን  ከግለ-ሠብ እንደሚመነጭ ተረድቶ ከዚያ ጋር የተመጣጠነ አክብሮት ሊሰጠው ይገባል' ለሁሉም ዜጎች ፍትሐዊ ለመሆን የተዘጋጀ፤ እያንዳንዱንም ግለ-ሠብ እንደባልንጀራ የሚያከብር፤ ሌላው ቀርቶ ጥቂቶች ገለል ብለው መኖር ቢመርጡ እንèን ያልተገባ ነገር አድርጎ የማይቆጥር፤ በጉዳያቸው ጣልቃ የማይገባ፤ ለምን በኔ አልታቀፉም የማይል እና በአጠቃላይ የባልንጀርነትንና የወገንተኝነት ሃላፊነቱን እንደሚገባ የተወጣ መንግሥት በማለም ሐሤት አደርጋለሁ' እንዲህ ዓይነቱን ፍሬ ማፍራት የቻለ፤ ወዲያውም የበሰለውን ፍሬውን መተካት የቻለ፤ ለተሻለ ፍፁም፣ እና የበለጠ የተወደደ መንግሥት መንገድ ያዘጋጃል፤ የትም ዕውን ሆኖ ባላይም፤ የዘወትር ሕልሜ ይህ እና ይህ ብቻ ነው!


   ማስታወሻ*
1-  በወቅቱ ኮንኮርድ የወረዳ መቀመጫ ነበረች'
2-  የሲልቪዮ ፔሌኮን Le Mie Prigioni (1749-1854)
ለ8 ዓመታት የፖለቲካ እስረኛ ሆኖ ያሣለፈውን ለማመልከት፤ ወደ እንግሊዝኛ በ1833 ተተረጎመ'
3-  መንገደኛ'
4-  በግሪኮች አፈ-ታሪክ፣ ሙዚቃው ድንጋይን፣ ዛፍንና አራዊትን ሣይቀር የሚማርክ ሙዚቀኛ'
5-  ጆርጅ ፒል (1557?1597)፣ የአልቻዛር ጦርነት'
6-  የ1787 ሕገ-መንግሥት ፀሐፊዎች'
7-  ዳንዔል ዌብስተር (1782-1852)
ለአሜሪካ ምክር-ቤት የተደረገ ንግግር'
8-  ኮንፊዩሸስ መሆን አለበት (551-479፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት')